DEV / QA

We use cookies to ensure you have the best possible experience on our site. Cookie policy.

ስለ በአዋቂ ስደተኞች የእንግሊዝኛ ፕሮግራም

ብቁ ነዎት?

የተሻለ እንግሊዝኛ, የተሻለ ኑሮ
ለአዲስ ስደተኞች ነጻ የእንግሊዝኛ ትምህርት

ስለ  በአዋቂ ስደተኞች የእንግሊዝኛ ፕሮግራም
(Adult Migrant English Program) 

  • በአውስትራሊያ ውስጥ ለመኖር፣ ሥራ ለመሥራት እና ትምህርት ለመማር የሚጠቅም ተግባራዊ እንግሊዝኛ ትምህርት ይማሩ።
  • የመንግንሥት እና የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ይማሩ።
  • ልክ እንደ እርስዎ ገና ወደ አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጡ አዳዲስ ጓደኞችን ያግኙ።
  • ራስዎን ለሥራ ወይም ለከፍተኛ ትምህርት ያዘጋጁ እና መፃዒ ሕይወትዎ እንዴት እንደሚሆን ከወዲሁ ዕቅድ ያውጡ።

ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  • የቤተሰብ፣ የባለሙያነት፣ የሰብዓዊነት፣ የጋብቻ ወይም በሌላ መልኩ የተፈቀደጊዜያዊ ቪዛ አልዎት።*
  • በእንግሊዝኛ መናገር/ማንበብ/መጻፍ አይችሉም ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎችን ማሻሻል ይፈልጋሉ።
  • ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በላይ ነው። ዕድሜያቸው ከ 15 እስከ 17 የሚሆን አንዳንድ ታዳጊ ወጣት ስደተኞችም ብቁ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል።

*የተፈቀዱ ጊዜያዊ ቪዛዎች የሥራ እና የዕረፍት ቪዛን፣ የሥራ የዕረፍት ቪዛ ወይም የጎብኚ ቪዛዎችን እንደማያካትቱ እባክዎ ልብ ይበሉ።

 እንደ አስፈላጊነቱ ሊስተካከል የሚችል የመማር አማራጭ 

  • በመላ ኲዊንስላንድ በሚገኙ መማሪያ ማእከላት ውስጥ በሙሉ ጊዜ ወይም በትርፍ ጊዜዎ ይማሩ።
  • ሙሉ ጊዜ ሰጥተው መማር የማይችሉ ከሆነ በበጎ ፈቃደኛ የቤት ውስጥ አስተማሪ ድጋፍ ያግኙ።
  • በርቀት ትምህርት በኩል በመስመር ላይ (በኢንተርኔት) ይማሩ።

 በመማሪያ ክፍል ውስጥ ምን እማራለሁ?

  • ከእርስዎ የእንግሊዝኛ ችሎታ ጋር በሚመጣጠን መማሪያ ክፍል ውስጥ ገብተው ይማሩ።
  • ትምህርቱን በሚማሩበት ጊዜ በማኅበረሰብ ጉዳይ አስፈጻሚ ሹሞች እና በእርስዎ የ AMEP ኬዝ ማናጀር አማካይነት ድጋፍ ያግኙ።
  • ስለ የአውስትራሊያ የሥራ ቦታ ቋንቋ፣ ባሕል እንዲሁም ልማድና ትውፊቶች ይማሩ።
  • በእርስዎ የመማር ችሎታ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ከዚህ ቀደም ውስን የሆነ የትምህርት ዕድል ከነበርዎት ተጨማሪ የእንግሊዝኛ ትምህርት በግል አስጠኚ አማካይነት ይማሩ።
  • እርስዎ እንግሊዝኛ በሚማሩበት ጊዜ ለልጅዎ ነጻ የሕፃን ክብካቤ ያግኙ (ብቁ ከሆኑ ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት)።
  • ለሥራ ቃለ መጠይቆች ራስዎን ያዘጋጁ እና ራስዎን የሚገልጽ አጭር ማመልከቻ (ሬዝዩሜ) ይጻፉ።

 ስለ የእኛ የእንግሊዝኛ ትምህርቶች አሁን ጥያቄዎችን ይጠይቁ

 Enquire now about our English lessons